Om የቅምሮች እና የቀስቶ ሥፍሮች ሥነ-ስሌት
በዚህ መጽሐፍ የምንመለከተው በዋነኛነት የቅምሮች እና የቀስቶ ሥፍሮች ሥነስሌት ነው። መጽሓፉ ስምንት ምዕራፎች አሉት። የመጀመሪያው ምዕራፍ የሥነቅምርን ብያኔ ፣ ዐይነቶች እና ካርተሳዊ የቅንብር ሥርዓትን ይመለከታል። ሁለተኛው ምዕራፍ የቀስቶ ሥፍሮችን ብያኔ እና ሥነስሌት ይመለከታል። ሦስተኛው ምዕራፍ የዐሪካት ሥነስሌትን ይመለከታል። በዐራተኛው ምዕራፍ ለብዙ ሥሌቶች ጠቃሚ የሆኑ እና ዐሪካትን በምጥን ሒሳባዊ ሐረግ ለማስቀመጥ ምቹ የሆነው የመወስቅ ሥነስሌት ባጭሩ ቀርቧል። ምዕራፍ አምስት በከርቦች የተለያዩ ነጥቦች ላይ የሚሆኑ ተዳፋትን ፣ ተቃናትን ፣ ቅርበትን (ጥጌትን) ፣ ተቃረብን ፣ ከፊል እና ሙሉ ልውጠትን ለማስላት የሚጠቅሙ የስሌት ዘዴዎችን ይመለከታል። ምዕራፍ ስድስት የሬይማንን ድምር ፣ ሥነአልዶትን እና የአልዶት መተንተኛ መንገዶችን ባጭሩ ያቀርባል። ምዕራፍ ሰባት የቀስቶ መስኮችን ልውጠት እና አልዶት አተናተን እና በዚሁም ውስጥ ጠቃሚ የሆኑትን የግሪንን እና የጋውስን አዋጆች ያቀርባል። በመጨረሻው ምዕራፍ የከፍታ ፣ የዝቅታ እና የምጣኔ ስሌቶች ባጭሩ ቀርበዋል።
Visa mer